ኣቢይ ኣሕመድ ዓሊ፥ኣስተዳደግ የበደለው ኣደገኛ አምባገነን
(ዶ/ር ብርሃነ ወልደሚካኤል 25/03/2026)
ይህ ኣጭር ድርሰት በኣማርኛ የተጻፈው ስለ ኣገራቸው በሚያስቡ ኢትዮጵያውያን እንዲነበብ በማሰብነው።
ኣቢይ ኣሕመድ ዓሊ የተደበላለቀ ኣስተሳሰብ ያለው ሰው ነው።ይህ የኣስተሳሰብ ድብልቅ ከአስተዳደግ የመነጨ መሆኑ ከመገመት በላይ ሆኖ ተገኝተዋል።
ኣሁን ማወቅ እንደተቻለው፡ኣቢይ ኣሕመድ በመሸታ ቤት ያደገ፣እውነተኛ ኣባቱ በእርግጥ ለማወቅ ያልቻለ እና ያልታደለ ሰው ነው።ኣሕመድ ዓሊ የተባሉ ሰው የእንጀራ አባት ዓይነት እንጂ በስጋ ግኑኝነት
እንዳልነበራቸው መረጃ ወጥተዋል።
በመሸታ ቤት ማደግ ራሱ የቻለ የአእምሮ ችግር የሚያስከትል ሁኔታ እንዳለው ኣያከራክርም።እንደዛ ሆኖም፡ኣቢይ ኣሕመድ በተፈጥሮ የላቀየ ጭንቅላት ብልህነት የታደለ ሰው ነው።ከእናቴ ተነገረኝ የሚለው የኢትዮጵያ ሰባተኛ ንጉስ ለመሆን በራሱ ውስጥ ገብቶበት ለመተግበሩ የእድሜ ልክ ጥረት እንዲያሳካ ኣድርጎታል።
የኢትዮጵያ ሰባተኛ ንጉስ ለመሆን ኣቢይ ኣሕመድ ተፈጥራዊ ብልህነቱ በመጠቀም ያደረገው የሚያስገርም ጥረት በብዙ መንገድ ሊገለጥ ይችላል።
ለምሳሌ፡ የሚከተሉትን ማየት ይቻላል፡
ሀ) በኢሃደግ ዘመን ወታደር ሆኖ በስልጣን የነበሩ ሃላፊዎች ትግርኛ ተናጋሪዎች ስለነበሩ የትግርኛ ቋንቋ ማወቅ ኣለብኝ ብሎ ጥሮ ከጥሩ በላይ የመናገር ችሎታ አዳብረዋል።የትግራኛ ቋንቋ ችሎታው እጅግ የሚደነቅ ነው።
ለ)ኣቢይ ኣህመድ ሲያድግ የኢስላም ሃይማኖት ተከታይ ሆኖ ነበር።የሚገርመው ነገር ግን፡የእስላም ሃይየማኖት ተከታይ ሆኜ የኢትዮጵያ ንጉስ ለመሆን ኣልችልም ብሎ ኣስቦ ወታደር ቤት ሲገባ እንደ ክርስትያን ሆኖ ነው።
ውትድርና መግባቱም ለንግስነት መድረሻ ዕላማ እንደሆነ መገመት ኣያዳግትም።
ሐ)ኣቢይኣሕመድ ከፋ ጠቅላይ ግዛት ተወልዶ ያደገ በመሆኑ ኦሮሞ ነው።
ኦሮሞዎች በኢትዮጵያ በህዝብ ብዛት ያላቸው ብሔር ቢሆኑም፡ ቁጥራቸው ለብቻው ወደ ስልጣን የሚያደርስ ኣይደልም።
ስለዚህ ኣቢይ ኣህመድ የኣማራ ድጋፍ በማግኘት ነው ወደ ንግስነት ልመጣ የምችለው የሚል ግንዛቤ ኣስቀድሞ የደረሰበት ሃሳብ ነው።
ለዚህ ሃሳብ ለማጠናክር ሲልም ኣንዲት ጎንደሬ የሆነች ሚስት ማግባት ጠቃሚ ሆኖ ነው ያገኘው።
መ)ኣቢይ ኣሕመድ የትምህርት ደረጃው ለማሳደግ ያደረገው ጥረት እጅግ ምየሚደነቅ ነው ምንም እንኳ በተለመደ መንገድ በመከተል ባይሆንም።ከሰባተኛ ክፍል እንዴት አድርጎ የዩኒቨርሲቲ ደረጃ የሚያክል ትምህርት የዶክተሬት መኣርግ ለማግኘት በቃ ብዙ ያነጋገረ ጉዳይ ነው። እንዲሁም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታዉም ቢሆን የላቀ ጭንቅላት እንዳለው የሚያመለክት ነው።
ስለዚህ፣ኣቢይ ኣሕመድ ተፈጥራዊ ችሎታ እንዳለው ግልጽ ቢሆንም ወደ ግላዊ የንግስነት ህልም ለመድረስ ብቻ የሚያውለው በመሆኑ ነው የሱ ችግር።ይህን ካልን በኋላ፣ኣቢይ ኣሕመድ እንዴት ዓይነት የላቀ የመታለያ ስልት ተጠቅሞ ወደ ስልጣን እንደመጣ ማያቱ ተገቢ ነው።
በኢሃደግ ዘመነ-መንግስት ኣቢይ ኣሕመድ ከባዶ ተነስቶ ኣስከ ሚኒስተር ደረጃ ደርሶ ነበር።በአንድ ወቅት ሃላፊዎቹ የነበሩ በስራው ስላልተደሰቱ፣ ወረኛ ሰው ሆኖም ስላገኙት፡ ኣባርረው ወደ ኦሮሞ ኣስተዳደር ነው የወረወሩት።
የንግስነት ህልም ከኣቢይ ኣስተሳሰብ የማይለይ በመሆኑ ግን በኦሮሞ ኣስተዳደር ሳለ ኣንድ ለማ መገርሳ የሚባል ጅል የሆነ ሰው አግኝቶ መጫወቻ ኣደረገው።ኣቢይ አሕመድ የተጠቀመበት የመሰላል ስልት የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ወደ ስልጣን መምጣት ግዜው ኣሁን ነው የሚል ስነ ሃሳብ ነበር።የሃበሻ ብሔሮች፡ለሶስት ሺ ዓመት ሲገዙ ቆይተው ኣሁን ደግሞ ኦሮሞች እንደዛ በቀጣይ፡ ለሶስት ሺ ዓመት መግዛት ኣለባቸው የሚል ሃሳብ ነበር። በዚህ ጥረት ለለማ መገርሳና ለሌሎች የኦሮሞ ልሂቃን በማሳመን ለግዝየውም ቢሆን እሱ ይያዘው ብለው ለቀውለታል። በኦሮሞ ህዝብ የገነፈለ ኣድማ የማይቀለበስ መሆኑን ተገንዝቦ የወቅቱ ጠቅላይ ምኒስተር ሃለማርያም ደሳለኝ ስልጣን ለኣቢይ አህመድ እንዲያስረክብ ተገደደ።
ከንግዲህ ወዲህ ኣቢይ የተረከበው ስልጣን ለማጠናከር ሲል፣በኣንድ በኩል ፍቅር እና መደመር የሚባሉትን ኣሳቦች በማራመድ ኣብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ከፈጣሪ የተላከ መልእክተኛ እንደሆነ ኣድርጎ ተቀበለው።
ነገር ግን፡በዛ በዋዜማው ግዜም ቢሆን ኣቢይ ለስልጣን ያሰጉኛል የሚላቸው ሰዎች መግደል እና ማሰር ተያይዞት ነበር።ተታለው ወደ ስልጣን ያደረሱት እንደ ለማ መገርሳ ሳይቀሩ ኣደጋ ላይ ወድቀው በተለያየ ሁኔታ ከእገር ተባረው እንዲወጡ ተደረገ።
የኣቢይ ከፍተኛ የስልጣን ጥማት እንዴት የዕድሜ ልክ ጥረት ሆነ ይቀጥላል ወደሚል ስልት ተሻግሮ ኣሁን ኣገሪትዋ ወድቃበት ወደ ኣለችው የአርስ-በርስ መፋጀት ደረጃ እንድትደርስ ኣድርጎኣታል።
ከታሪክ የተማርነው ነገር ቢኖር፣ ኣምባገነኖች ስልጣን ላይ ተቆንጥጠው ለመኖር ማንኛውም ነገር ለማድረግ፣ማለትም ህዝብ ቢያልቅ ኣገር ችግር ውስጥ ብትወድቅም፣ደንታቸው አይደለም።
አብይ ኣህመድ ደግሞ እንዲያውም የከፋ ኣምባገነን ነው።በትግራይ የፈጸመው ኣስከፊ ጀኖሳይድ፣በኦሮምያ እና በአማራ ክልሎች እየተካሄደ ያለው የሰው እልቂት ለአቢይ ደንታ የሚሰጡ ኣይደሉም።ኣሰብ የሚባለው ትረካም ቢሆን ለኣገር ይጠቅማል ብሎ በመቆርቆር ሳይሆን በኣንድ በኩል ህዝብ ይስብልኛል በማለት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ለኢሜሬቶች ጥቅም ሲል የሚያደርገው ያለው የእብደት ዘመቻ ነው።
ኣጽኖታዊ ማስጠንቀቅ ያለ ሚመለከታቸው ሁሉ
ኣቢይ ኣሕመድ በቀላሉ ሊገመት የማይገባው በጣም ኣደገኛ ሰው ነው። ዓለም ሳይቀር ኣታሎ የኖቤል ሽልማት ያገኘ ሰው እኮ ነው።ኣደጋኝነቱ፣የሌላ ኣገር ሰራዊት በማሳተፍ በገዛ ኣገሩ በፈጸመው ጀኖሳይድ እጅግም የባሰ ኣምባገነን ሰው መሆኑ በቂ ማስረጃ ነው።
ስለዚህ፣የኢትዮጵያ ህዝብ በፈለገው መዋቅር መኖር መብቱ መሆኑ ሊታምንበት ይገባል።በዚህ ኣኳያ ብቻ ነው የኢትዮጵያ ህዝቦች የእርስ በርስ መተባበር ሊያደርጉ የሚችሉ።አንድ ብሄር በሌሎች ብሄሮች የበላይነት ይዤ እገዛለሁ የሚል ኋላ ቀር ኣስተሳሰብ ለማስወገድ የሰላም ወዳጅ ሁሉ ጥረት ማድረግ ያስፈልገዋል።ይህ ማለት የሰው ህይወት ዋስትና ቀዳሚነት መስጠት ስለ ሚገባነው።ስለዚህ ኣቢይ ኣህመድ የህዝብ ልዩነት በመጠቀም የስልጣን ኮረቻ ላይ ተቆናንጦ ለመኖር ተጨማሪ ዕድል በምንም መልኩ መሰጠት የለበትም።
ጥልቅ ኣስፈላጊነት ጸሎት ለፈጣሪ
የፈጣሪ ስራ ስዉር ነው የሚባል ኣነጋገር ኣለ።ይህን በመካከለኛው ምስራቅ የሚካሄደው ያለው ጦርነት ምናልባትም ለዚህ ኣባባል እውን የሚያደርግ ሊሆን ይችላል።ኣቢይ ኣሕመድ የሚያደርጋቸው ድንፋታዎች ለኢሜሬቱ ቢንዛይድ ተማምኖ እንደሆነ ዘርፈ-ብዙ ማስረጃዎች 3?!3?አሉ።
ሆኖም፣ኢሜሬት የኢስራኤል እና የኣመሪካ ጥገኛ በመሆንዋ ከኢራን በዘነበው ሚሳይሎች የራስዋ የመኖር እጣ ፈንታም ኣስጊሆኖባታል።
ስለዚህ፡ይህ የፈጣሪ ስዉር ስራ ሆኖ በኢትዮጵያ የህዝብ የእርስበርስ መተላለቅ ሳያስከትል ኣገሪትዋ ከኣንባገነኑ ኣቢይ ኣሕመድ እንድትገላገል ፈቃዱ እንዲሆን መጸለይ ያስፈልጋል።
ተፈጸመ።




